አሮጌው 2014 አመት ተገባዶ አዲሱ የ2015 አመት መግቢያ ዋዜማ ላይ የኢትዮጵያ አንድነት ቀን በሚል ጳጉሜ 5/ 2014 አንድነታችን በዘመናት አብሮነታችን የተገነባ እሴታችን ነው በሚል መሪ ቃል በሮም የኢትዮጵያ ኤምባሲ አዘጋጅነት በርካታ ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን በተገኙበት በደማቅ ሁኔታ ተከብሯል።
በዕለቱም በወቅታዊው የሀገራቸውን ጉዳይ አስመልክቶ ውይይት ተደርጎበታል። በ2014 ዓ.ም እንደሀገር ብዙ ፈተናዎችና ስኬቶች የተመዘገቡበት መሆኑ በውይይቱ የተነሳ ሲሆን መጪው 2015ዓ.ም አመት ሁሉም ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ከዘርና ከሃይማኖት ልዩነቶች ነፃ ሆነው በሀገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ ከሀገርና ከህዝብ ጎን መቆም እንዳለባቸው ጥሪ ተደርጎላቸዋል ።
በዝግጅቱ ላይ የታደሙ ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ለአገራቸው አንድነትና ብልጽግና የበኩላቸውን ድርሻ ለመወጣት ዝግጁ መሆናቸውን ገልፀዋል::
በተጨማሪም በሀገራችን በተከሰቱ ጦርነትና ግጭቶች ከቤት ንብረታቸው የተፈናቀሉ ዜጎችን ለመርዳት ለሚደረገው እንቅሰቃሴ ድጋፍ ለማሰባሰብ እንዲሁም የታላቁን ህዳሴ ግድብ ግንባታን ለማጠናቀቅ ቦንድ በመግዛት የበኩላቸውን እንደሚወጡ ቃል ገብተዋል።
May be an image of 3 people and people standingMay be an image of 10 people, people sitting, people standing and indoorMay be an image of 12 people, people sitting and people standingMay be an image of 5 people, people standing and outdoors
Twitter
Facebook
Instagram