“ሰንደቅ ዓላማችን የብዝሃነታችን መገለጫ የሉዓላዊነታችን ምሰሶ ነው!” በሚል መሪ ቃል ለ15ኛ ጊዜ በብሄራዊ ደረጃ እየተከበረ የሚገኘው የሰንደቅ አላማ ቀን ክብርት አምባሳደር እና መላው የሚሲዮኑ ሰራተኞች በተገኙበት በሚሲዮኑ ቅጥር ግቢ ተከብሯል።
በስነ-ስርዓቱ ላይ ክብርት አምባሳደር ደሚቱ ሐምቢሳ ስለ ሰንደቅ ዓላማ አከባባር እና ክብር እንዲሁም ስለ እለቱ መሪ ቃል ንግግር አድርገዋል።
በመጨረሻም ሰንደቅ ዓላማ በመስቀል እና ብሄራዊ መዝሙር በመዘመር እንዲሁም ከሰንደቅ ዓላማ ፊት ቃለ መሃላ በመፈፀም ተጠናቋል።
Twitter
Facebook
Instagram