ክብርት አምባሳደር ደሚቱ ሀምቢሳ ከሰሜን መቄዶንያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከሆኑት ክቡር Bujar Osmani ጋር ስለ አገራችን ወቅታዊ ሁኔታ እና የሁለትዮሽ ግንኙነት ማጠናከር በሚቻልባቸው መስኮች ዙሪያ ተወያይተዋል::
በውይይቱ መንግስት በአገሪቱ ሰላምን ለማስፈንና ለሰላማዊ አማራጮች ያሳየውን ቁርጠኝነት እንዲሁም እርዳታ ለህብረተሰቡ እንዲደርስ የተከናወኑ ተግባራትን አስረድተዋል::
ሚኒስትሩ በመንግሥት በኩል ሰላምን ለማስፈን የተከናወኑ ተግባራት የሚበረታቱ መሆናቸውን ገልጸዋል:: በቀጣይም የሁለትዮሽ ግንኙነቱን ለማጠንከር በቅርበት ለመስራት ከስምምነት ላይ ተደርሷል::