Power of Attorney

የውክልና ስልጣን አገልግሎት

እርስዎን ወክሎ በኢትዮጵያ ውስጥ ጉዳዮችን የሚከታተል ሰው(ዎች) ወይም ተወካይ ለመሾም ከፈለጉ የውክልና ስልጣን ያስፈልግዎታል።

በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ስር በዓለም ዙሪያ በኢምባሲና ቆንጽላ ጽህፈት ቤት በኩል የሚሰጡ የውክልና ስልጣን አገልግሎት የኦንላይን አገልግሎት መስጫ አማራጮችን አቅርቧል። በመሆኑም የኦንላይን አገልግሎትን https://digitalmofa.com ማግኘት የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን። 

የዲጂታል የኦንላይን ውክልና መተግበሪያን በ iOS እና Android ማውረድ ይችላሉ።

በኢምባሲው ቆንስላ ፅ/ቤት አገልግሎቱን ማግኘት ለምትፈልጉ:-

ለኢትዮጵያዊያን

      • ፓስፖርት ኦርጅናልና ኮፒ (የአገልግሎት ጊዜው ያላለፈት ቢያንስ የ6 ወር ጊዜ ያለው)
      • የመኖርያ ፍቃድ / ፐርሜሶ ዲ ሶጆርኖ ኦርጅናልና ኮፒ
      • ካርታ ዲ ኢዴንቲታ ኦርጅናልና ኮፒ
      • የተወካይ የቀበሌ መታወቂያ ኮፒ (የተወካይ ሙሉ ስምና አድራሻ የሚታይ)
      • የአገልግሎት ክፍያ 61 ዩሮ

ለትውልድ ኢትዮጵያዊያን

      • ፓስፖርት ኦርጅናልና ኮፒ
      •  የትውልድ ኢትዮጵያ መታወቂያ ኦርጅናልና ኮፒ (የአገልግሎት ጊዜው ያላለፈት ቢያንስ የ6 ወር ጊዜ ያለው)
      • ካርታ ዲ ኢዴንቲታ ኦርጅናልና ኮፒ
      • የተወካይ የቀበሌ መታወቂያ ኮፒ (የተወካይ ሙሉ ስምና አድራሻ የሚታይ)
      • የአገልግሎት ክፍያ 61 ዩሮ
Twitter
Facebook
Instagram