ByWebsite

Jul 23, 2024
ክቡር አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ ከጣሊያን የኢንተርፕራይዞችና ሜድ ኢን (made IN )ጣሊያን ምክትል ሚኒስትር ጋር ተወያዩ ።
=========
(ሐምሌ 12 ቀን 2016): በሚላን፣ ጣሊያን ከተካሄደው የኢትዮ-ጣሊያን የቢዝነስ ፎረም ጎን ለጎን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ ከጣሊያን የኢንተርፕራይዞችና ሜድ ኢን (made IN) ጣሊያን ምክትል ሚኒስትር ከሆኑት ክቡር ቫለንቲኖ ቫለንቲኒ ጋር ተወያይተዋል።
ክቡር ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለው ዘርፈ ብዙ ግንኙነት እየተጠናከረ መምጣቱን ጠቅሰው፥ ለዚህም በሁለቱ ሀገራት መሪዎች ደረጃ የተደረጉ ጉብኝቶች እና ምክክሮች የላቀ አስተዋጽኦ ማበርከታቸውን ገልጸዋል።
በሀገራቱ መካከል የተፈረሙ በርካታ የትብብር ስምምነቶች መኖራቸውን ያወሱት ክቡር ሚኒስትር ዴኤታው የ2023-2025 የትብብር ማዕቀፍ ስምምነት ተጠቃሽ መሆኑን ገልጸዋል።
ሁለቱ ወገኖች በኢትዮጵያ እና ጣሊያን መካከል ያለውን ኢኮኖሚያዊ ግንኙነት ለማጠናከር በአቅም ግንባታ እና በቴክኖሎጅ ሽግግር ዙሪያበአነስተኛ እና መኸከለኛ እንዱስትሪ ዘርፍ ለወጣቶች የስራ እድል ፈጠራ ላይ ትኩረት ተሰጥቶ በምሰራበት ላይም ተወያይተዋል::
በተያያዘም የጣሊያን መንግስት ከአፍሪካ ሀገራት ጋር የጋራ ልማት ለመካሄድ ይፋ ያደረገው የልማት ትብብር ማዕቀፍ የሆነው የማቲ ፕላን ኢትዮጵያ የቅድሚያ ተጠቃሚ እንደመሆኗ መጠን ትግበራውን አጠናክሮ ለማስቀጠል ተስማምተዋል።
በተጨማሪም ክቡር አምባሳደር ምስጋኑ በኢትዮጵያ ኢንቨስት ለማድረግ ፍላጎት ካሳዩ መልህቅ ኢንቨስተሮች ጋር በመገኘት በኢትዮጵያ ያለውን ምቹ የኢንቨስትመንት ዕድሎች በተመለከተ ማብራሪያ ሰጥተዋል።
Twitter
Facebook
Instagram