ሚሲዮናችን በሚገኝበት በጣሊያንና በምንሸፍናቸው በግሪክ፣ በማልታ እና በሳይፕረስ ከሚገኙ ዳያስፖራዎች ጋር በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ተደረገ ፣
=========================

እ.ኤ.አ ኦገስት 11 ቀን 2024 ዓም በሮም የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ኤምባሲ አዘጋጅነት በጣሊያን ኤምባሲያችን ተቀማጭ በሆነበትና በሚከታተላቸው አካባቢዎች ለሚኖሩ የዲያስፖራ ማህበረሰብ አባላት በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ ከክብርት አምባሳደር ደሚቱ ሀምቢሳ ጋር የበይነመረብ ውይይት ተካሄዷል።

ውይይቱም ወቅት በአገራችን እየተከናወኑ  ያሉትን መጠነ ሰፊ የልማት፣ የሰላም እና የዴሞክራሲ ስረዓት ግንባታን አስመልክቶ ማብራሪያ ተሰጥቶአል:: በአሁኑ ወቅት መንግስት ዳያስፖራውን ከአገሩ ጋር ለማስተሳሰር የሚያስችል እቅዶችን በመንደፍ እያደረገ ያለውን ጥረት  አበራታች መሆኑን ተሳተፍዎች አንስተዋል።

ህዳሴ ግድብ የመጨረሻ ምዕራፍን ለማገባደድ  የቦንድ ግዥ  የጋራ መግባበት ላይ ተደርሶአል::

Twitter
Facebook
Instagram