የፌዴራል ቤቶች ኮሮፓሬሽን በጣሊያን ሮምና ሚላን ከሚኖሩ ዳያስፖራዎችና በጣሊያን ለቤት ግንባታ የሚሆኑ ቴክኖሎጅ ከአላቸው ካምፓኒ ጋር ተወያዩ::

=====================

(ሀምሌ 15 ቀን 2016 ዓ.ም) በሮም የኢ.ፌ.ዲሪ ኤምባሲ አመቻቺነት የፌዴራል ቤቶች ኮሮፓሬሽንበጣሊያን፣ ሮምና ሚላን ከሚኖሩ ዳያስፖራዎችና በጣሊያን ለቤት ግንባታ የሚሆን ቴክኖሎጅ ከአላቸው ካምፓኒዎች ጋር ውይይቶችን

አድርገዋል፡፡

የፌደራል ቤቶች ኮርፓሬሽን ከለውጡ በፊት ለሰራተኞቹ እንኳን ደመወዝ መክፈል ከማይችልበት ኪሳራ፣ ከኃላ ቀር አሰራር እንዲሁም ከተመሳሳይ ዘርፈ-ብዙ ችግሮች ተላቆ ባለፉት ስድሰት አመታት በስኬት ጎዳና ላይ እንደሆነ የኮርፕሬሽኑ ዋና ስራ አስፈፃሚ የሆኑት ክቡር አቶ ረሻድ ከማል ገልጸዋል። ዋና ስራ አስፈጻሚው በጣሊያን በሮምና በሚላን ከሚኖሩ ኢትዮጵያዊያንና ትውልድ-ኢትዮጵያዊያን ጋር በነበራቸው መድረክ የፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽን በአጭር ጊዜና በዋጋ ተወዳዳሪ የሆነ የቤት ግንባታ ልምድ ማዳበሩን ጠቅሰው፣ በየጊዜው እያደገ ያለውን የዜጎች የቤት ፍላጎት ታሳቢ ያደረገ የቤት ግንባታ ፕሮጀክት ተግባራዊ እየተደረገ መሆኑን አክለው ገልጸዋል። በቀጣይ በውጭ ሀገር የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ያማከለ የቤት ግንባታ ለማስጀመር የህግ-ማዕቀፍ፣ የቤት ዲዛይን፣ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ስለሚኖረው ቁጠባና የብድር አገልግሎቶችና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች ጋር የተገናኙ የቅድመ-ዝግጅት ስራዎች በመጠናቀቅ ላይ መሆናቸው ተገልጿል።

 

በሮም የኢትዮጵያ ኤምባሲ ልዩ መልዕክተኛና ባለሙሉ ስልጣን የሆኑት ክብርት አምባሳደር ደሚቱ ሐምቢሳም ባደረጉት ንግግር የፌደራል ቤቶች ኮርፓሬሽን ዳያስፖራውን የሚያሳተፍ የቤቶች ልማት ፕሮጀክት ለመጀመር መዘጋጀቱ በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ከሀገራቸው ጋር በልማት እንዲተሳሰሩ የበኩሉን ሚና ስለሚጫወት የሚኖረው ፋይዳ ከፍተኛ መሆኑን ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የዳያስፖራ ቅርንጫፍ ማኔጀር የሆኑት አቶ ለማ ዋቄዮ በበኩላቸው በፌደራል ቤቶች ኮርፓሬሽን ለሚጀመረው የዳያስፖራ የቤቶች ልማትና በሌሎች በዳያስፖራ በኩል ለሚቀርቡት የኢንቨስትመንትና የተለያዩ ፕሮጀክቶችን ብድር ማቅረብ እንደምችልም አብራርተዋል።

የውይይቱ ተሳታፊዎችም በበኩላቸው በኮሮፓሬሽኑ እየተመዘገበ ባለው ለውጥ መደሰታቸውን ገልፀው፣ ቤት ፕሮጀክት ላይ ለመሳተፍ ዝግጁ መሆናቸውን ገልፀዋል።

 

በሌላ በኩል የፌዴራል ቤቶች ኮርፓሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ የተመራው ልኡካን ቡድን ቀድሞ በኤምባሲው በተመረጡ በቤት ግንባታ ላይ አዳድስ ቴክኖሎጅ ካላችው ኩባኒያዎች ጋር አብሮ ለመስራት የሚያስችል መግባባት ላይ የደረሱ ሲሆን የካፓኒዎችንም ስራ ተዘዋውረው ጎብኝተዋል።

Twitter
Facebook
Instagram