የአገራችንን ባህላዊ እሴቶችና የጥበብ ስራዎችን ማስተዋወቅ  ተቻለ፣
================
 በሮም ተቀማጭ የሆኑ የBRICS አባል አገራት ኤምባሲዎች  ከሩስያ የባህል ማዕከል ጋር በመተባበር  በተዘጋጀው ኢግዚቢሽን ላይ የአገራችንን የቡና አፈላል ስነ-ስርዓት፣  አብሮነት ኦና ባህላዊ ሙዚቃ መሳሪያችንን የሚያሳይ የጥበብ ስራ በማቅረብ ከማስተዋወቅ በተጨማሪ ኢትዮጵያ የበርካታ ታሪክ፣ ባህልና አለም አቀፍ ደረጃቸውን የጠበቁ  የቱሪስት መዳረሻ ባለቤት እንደሆነችም ሚሲዮኑ አስተዋዉቋል።

በዕለቱ የኤምባሲው ምክትል ሚሲዮን መሪ አቶ አሰፋ አብዩ  አገራችን ኢትዮጵያ ብሪክስን በቅርቡ ከተቀላቀሉት አገሮች አንዷ መሆኗን፣ ከብዙዎቹ የብሪክስ አባል ሀገራት ጋር ለጋራ ጥቅም ለጠንካራ ኢኮኖሚያዊ እና የባለብዙ ወገን ግንኙነቶች እንዲረጋገጥ አስተዋፅዖ የምታደርግ ሀገር መሆኗን ገልጸው፥  BRICS ዓለም አቀፉን ሥርዓት በማጠናከር እና በማሻሻል ውስጥ ወሳኝ ሚና የሚጫወት፣  አካታች እና ሚዛናዊ ዓለም አቀፍ ስርዓት ለመፍጠር ያለውን ፍላጎት አገራችን እንደምትደግፍ ገልጸዋል።

መድረኩ በሮም የሩሲያ የባህል ማእከል  አስተባባሪነት የተዘጋጀና የአባል ሀገራቱን የጥበብ ስራዎች ለማስተዋወቅ፣ ግንኙነትን በማጠናከር የBRICS አባል ሀገራትን ኤግዚቢሽን በጋራ ማዘጋጀት በመቻሉ የተሰማቸውን ደስታ ገልጸው።፤ አዲስ ለተቀላቀሉ ሀገራት ታሪክን፣ ኪነጥበብን፣ ቱሪዝም እና ባህልን ለሰፊው አለም ለማስተዋወቅ የበለጠ ጠቀሜታ ያለውና የአገራችንን ገጽታ ለመገንባት ያስቻለ መሆኑን ገልጸዋል

Twitter
Facebook
Instagram