ክብርት አምባሳደር ደሚቱ ሀምቢሳ በቆጵሮስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳየች ዳይሬክተር ጋር ተወያዩ።
====================
ተቀማጭነታቸው በሮም ሆኖ በሳይፕረስ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ልዩ መልዕክተኛና ባለሙሉስልጣን አምባሳደር ደሚቱ ሀምቢሳ ክብርት አምባሳደር ደሚቱ ሀምቢሳ በሳይፕረስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳየች ዳይሬክተር  ጋር  ከሆኑት Ms. Andrea Petranyi ጋር በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን የሁለትዮሽና የባለብዙ ወገን ግንኙነት የበለጠ ለማጠናከር በሚያስችሉ ጉዳዮች ዙሪያ በኒኮሲያ፣ ቆጵሮስ ተገናኝተው ውይይት አድርገዋል።

በወቅቱም ሁለቱ ወገኖች በሁለቱን አገራት መካከል ያለውን ረጅም ጊዜ ያስቆጠረ እና ውጤታማ ግንኙነትን አውስተው፣  በአሁኑ ወቅቱም ግንኙነቱን የበለጠ ለማጠናከር  የሚያስችል ምቹ ሁኔታ መኖሩን አንስተዋል።

በሀገሪቱ መካከል በተለያዩ ዘርፎች ያለውን ግንኙነት የበለጠ  ለማጠናከር የኢትዮ-ቆጵሮስ የፖለቲካ ምክክር ለማካሄድ ስምምነት ለመፈራረም መግባባት ላይ ደርሰዋል።

በተያያዘም ክብርት አምባሳደር ከቆጵሮስ የንግድ ምክር ቤት ዋና ጸሐፊ ከሆኑት Marios Tsiakkis ጋር በመገናኘት በሁለቱ ሀገራት የንግድ ማህበረሰብ መካከል ያለውን ግንኙነት ለማጠናከር በተለይም በሁለቱ ሀገራት የንግድ ምክር ቤቶች መካከል  የጋራ ትብብር ለማድረግ የሚያስችል የጋራ መግባቢያ ስምምነት ለመፈራረም እንዲሁም በሀገራችን የቅድመ ኢንቨስትመንት ጉብኝት ለማካሄድ ስምምነት ላይ ደርሰዋል።

Twitter
Facebook
Instagram