በጣሊያን ሮም እና አካባቢዋ ከሚገኙ የዳያስፖራ አባላት ጋር በታላቁ የህዳሴ ግድብ ግንባታ ዙሪያ ውይይት ተደረገ ፣
=========================
(መስከረም 12 ቀን 2017 ዓ.ም ):በሮም የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ኤምባሲ አዘጋጅነት በጣሊያን ሮም እና አካባቢዋ ለሚኖሩ የዲያስፖራ ማህበረሰብ አባላት ታላቁ ህዳሴ ግድብ የደረሰበትን ደረጃ እና ለቀሪ ስራዎች የሚያስፈልግ ድጋፍ በተመለከተ ክብርት አምባሳደር ደሚቱ ሀምቢሳ ለታዳሚዎች ገለፃ አድርገዋል።
 
በገለጻቸው በአገር ደረጃ መንግስት ሰላምን: ዲሞክራሲና ልማትን ለማረጋገጥ እየሰራ ያለውን ዘርፈ ብዙ እንቅስቃሴዎችና የተገኙ ውጤቶች ዙሪያ ገለጻ አድርገዋል :: በዋናነትም የታላቁ ህዳሴ ግድብ የመጨረሻ ምዕራፍን ለማገባደድ መንግስት ከፍተኛ እንቅስቃሴ እያደረገ መሆኑንና ለቀሪ ስራዎች ማስጨረሻ ኮሙኒትው ቦንድ እንድገዙ ጥሪ አቅርበዋል።
 
ተሰብሳቢዎቹም ግድቡን እንደ ጀመር ነው እንጨርሰዋለን በማለት በገቡት ቃል መሠረት በዛሬው እለትም የቦንድ ግዥ ፈጽመዋል::
Twitter
Facebook
Instagram