ክብርት አምባሳደር ደሚቱ በባዮፊውል ዘርፍ ስልጠናቸውን ላጠናቀቁ ኢትዮጵያዊያን ሰልጣኞች የምስክር ወረቀት ሰጡ
===================================

(ጥቅምት 7 ቀን 2017 ዓ.ም): ክብርት አምባሳደር ደሚቱ ከሀገራችን የተለያዩ ተቋማት የተውጣጡ እና በጣሊያን የኢነርጂ ኩባንያ Eni የስልጠና ማዕከል በባዮፊውል ዘርፍ የተዘጋጀውን ስልጠና ተከታትለው ላጠናቀቁ ሰልጣኞችን በኩባንያው የተዘጋጀውን የምስክር ወረቀት በስልጠና ማዕከሉ በመገኘት ሰጥተዋል።

በስልጠናው የመዝጊያ ስነ-ስርዓት ላይ ባስተላለፉት መልዕክትም በሀገራችን እና በጣሊያን መካከል በኢነርጂ ዘርፍ እየተደረጉ ያሉትን ዘርፈ ብዙ ትብብሮች አውስተዋል። ስልጠናው በሀገራችን የአማራጭ የኢነርጅ ልማት ተግባራዊ ለማድረግ እየተከናወኑ ላሉ ጥረቶች የራሱን አዎንታዊ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክት ያላቸውን እምነት ገልጸዋል።
አክለውም በሁለቱ ሀገራት መካከል መሰል የአቅም ግንባታ ዘርፎች ያለውን ትብብር የበለጠ አጠናክሮ ለማስቀጠል በሀገራችን በኩል ያለውን ዝግጁነት አረጋግጠዋል
 
H.E Amb. Demitu presented certificates to the Ethiopian trainees who completed their training in Biofuel.
================================
(October 17, 2024): H.E Amb Demitu Hambisa attended the closing ceremony of a capacity building training program on bio fuels organized by Eni, Italian Energy Company, for Ethiopians comprised from various Ethiopian institutions and presented certificates for successful completion of their training.
In her remark at the event, she mentioned the existing multifaceted cooperation between Ethiopia and Italy in the energy sector, and emphasized the positive contribution of the training to the ongoing efforts of Ethiopian government on alternative energy development.
She underlined the readiness of Ethiopian side to further strengthen the cooperation between the two countries in the areas of capacity building.
Twitter
Facebook
Instagram