በሮም ጊዜያዊ የገቢ ማሰባሰቢያ አስተባባሪ ኮሚቴ ተወካዮች ጋር በተለያዩ ወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች እና በቀጣይ በሶስተኛ ዙር የገቢ ማሰባሰቢያ የቅድመ-ዝግጅት ስራዎች ዙሪያ ክብርት አምባሳደር ደሚቱ ሀምቢሳ በተገኙበት ውይይት ተደርጓል።
ክብርት አምባሳደር ደሚቱ ሀምቢሳ፣ በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ ገለፃ አድርገውላቸዋል ቀጥለውም ኮሚቴዎቹ በሀገራችን በተለያዩ አከባቢዎች በተፈጠሩ ግጭቶችና ጦርነት ከቤት ንብረታቸው የተፈናቀሉትን ዜጎች መልሶ ለማቋቋም የገንዘብና የቁሳቁስ ድጋፎችን ሲያደርጉ እንደነበር አስታውሰው፣ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
የኮሚቴ ተወካዮችም በበኩላቸው በተለያዩ ግጭቶችና ጦርነት የተፈናቀሉ ዜጎችን ለመርዳት በዚህ አመት ሁለት ዙር የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራሞችን አስተባብረው ያሰባሰቡትን ገንዘብ ለኤምባሲው ገቢ ተደርጎ ለመንግስት መተላለፉን አስታውሰው፣ የዚሁ አካል የሆነውን ሶስተኛ ዙር በማዘጋጀት ላይ መሆናቸውን ተናግረዋል።
በሌላም በኩል ቀደም ሲል በሮም ተበታትነው የነበረውን የኢትዮጵያ ኮሙዩኒቲን ጠንካራና ወጥ ለማድረግ የተዋቀረው ኮሚቴ እስካሁን የሰራቸው ስራዎች የደረሰበትን ደረጃ ማብራሪያ ሰጥተዋል።
Twitter
Facebook
Instagram