በሮም የእርዳታ አሰባሳቢ ኮሚቴ በሀገራችን በጦርነት ከቤት ንብረታቸው ለተፈናቀሉ ዜጎች ማቋቋሚያ ያሰባሰቡትን 5914 ዩሮ የገንዘብ ድጋፍ በሮም የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ኤምባሲ ድረስ በማምጣት ገቢ አድርገዋል።
በዕለቱ ከኮሚቴ ጋር የተገናኙት ክብርት አምባሳደር ደሚቱ ሀምቢሳ ለተደረገው የገንዘብ ድጋፍ አመስግነው፣ በሀገራችን በጦርነት ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለው የወገኖቻቸውን እርዳታ ለሚጠባበቁ ዜጎቻችን ከዳያስፖራ የሚደረገው የገንዘብና የቁሳቁስ ድጋፎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ ጠይቀዋል።
ኮሚቴዎችም በበኩላቸው የተለያዩ የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራሞችን በማዘጋጀት ለተጎዱ ወገኖች ለመድረስ እንደሚሰሩ ቃል ገብተዋል።
 
Twitter
Facebook
Instagram