በሮም የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ኤምባሲ መስከረም 08 ቀን 2015ዓ.ም በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮችና በሀገራዊ የሀብት አሰባሰብ ጥሪ ዙሪያ በጣሊያንና በግሪክ ከሚኖሩ ከተለያዩ የሃይማኖት ተቋማት መሪዎችና ተወካዮች ጋር ክብርት አምባሳደር ደሚቱ ሀምቢሳ ውይይት አድርገዋል ::
በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ በተለይ በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል በነበረው ጦርነት ምክንያት የወደሙ ህዝባዊ ተቋማትን መልሶ ለመገንባትና ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለው የወገኖቻቸውን ድጋፍና እርዳታ የሚሹ ዜጎችን ለማቋቋም የገንዘብ እርዳታ ማድረግ በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ዙሪያ ማብራሪያ ተደርጎላቸዋል ::
የሃይማኖት አባቶችና ተወካዮችም በበኩላቸው የሀብት ማሰባሰብ ስራ በመስራት ሀገራቸውንና ወገኖቻቸውን ለመረዳት ዝግጁ መሆናቸው ገልጸው በቀጣይ ወደ ሀብት ማሰባሰቡ ስራ እንደሚገቡ ዝግጁነተቸውን ገልጸዋል::
Twitter
Facebook
Instagram