ክቡር ሚኒስትሩ በገለጻቸው ማዕቀፍ ትኩረት የሚያደርግባቸው አራት በተለዩ ምርቶች ስንዴ፣ ቡና፣ አቮካዶና የእንስሳት ተዋፆኦ መሆኑን ጠቅሰው በዋናነት በቡልቡላ እና ይርጋለም አግሮ-ኢንዱስትሪያል ፓርክ ማዕከላት ተግባራዊ እንደሚሆኑ አብራርተዋል::
 
በገለፃቸው መጨረሻም ኢትዮጵያ የብዙሀን ዜጎች ህይወት ለመለወጥ ግብርናው ዘርፍ ትኩረት ያደረጉ በርካታ ማሻሻያዎችን እያከናወነች የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥና ዘላቂ ልማትን ለማምጣት እየሰራች እንደምትገኝ ገልጸዋል::
 
ከዓለም ምግብ ፎረም ጎን ለጎን የእጅ ለእጅ የድጋፍ ማዕቀፍ (Hand in Hand initiative) ትግበራ አስፈላጊ በጀትና የልማት አጋሮችን ለመፍጠር ከተለያዩ የድርጅቶች ኃላፊዎች ጋር ውጤታማ ውይይት አካሄደዋል::
 
ክቡር ሚኒስትሩ ከዓለም ባንክ፣ CNH-Industrial, BAYER Group, International Seed Company, Blue Grass Partners, Mileutis ltd ጋር በጋራ መስራት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት አድርገዋል::
Twitter
Facebook
Instagram