ስምምነቱን በኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ በኩል የፈረሙት የግሩፑ ዋና ስራ አስፈፃሚ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ ናቸው:: በፊርማው ስነስርዓቱ ወቅት እንደገለፁት ሙሉ ፋብሪካው ኢትዮጵያ ውስጥ እንደሚቋቋም እና የቴክኖሎጂ ሽግግር በአቅም ግንባታና በሰው ኃይል ስልጠና ዙሪያ ላይ በጋራ እንደሚሰሩ ገልፅዋል:: የጣሊያኑ የፋሪሰን ኩባንያ ዋና ስራ አስፈፃሚ Mr. ጂያኮሞ በበኩላቸው ከኢትዮ ኢንጀነሪንግ ግሩፕ ጋር የደረሱት ስምምነት ትልቅ የገበያ እድል እንደሚከፍትላቸው ገልፀው ስምምነቱን ወደ ተግባር ለመቀየር ዝግጁ መሆናቸውን ገልፅዋል:: በፊርማ ስነስርአቱ ላይ የተገኙት በኢትዮጵያ የጣልያን ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ደሚቱ ሃምቢሳ ስምምነቱ የሁለቱ አገሮች የኢኮኖሚና ኢንቨስትመንት ግንኙነት ለማጠናከር ጉልህ ሚና እንደሚጫወት በመግለፅ የኢትዮጵያ የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ለማዘመንም ትልቅ ድርሻ ስለአለው ስምምነቱን ተግባራዊ ለማድረግ ኤምባሲው አስፈላጊውን ሁሉ ድጋፍ እንደሚያደርግ ገልፀዋል:: በፊርማ ስነስርአቱ ላይ የቪቼንሳ ግዛት የማእከላዊ መንግስት ተወካይ እና የቪቼንሳ ከተማ የቻምበር ፕሬዝዳንት ተገኝተው መልእክት አስተላልፈዋል::
Twitter
Facebook
Instagram