በጣሊያን የቪቼንሳ ግዛት የንግድ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት እንዲሁም የቪቼንሳ ከተማ የንግድ ማህበረሰብ አባላትና የኩባንያ ባለቤቶች በተገኙበት በጣሊያን የኢትዮጵያ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ክብርት ደሚቱ ሃምቢሳ በኢትዮጵያ ስላለው የኢቨስትመንት እድሎች በተለይም በማኑፋክቸሪንግ እና በኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ዘርፍ ያሉት ሰፊ አማራጮችና እድሎች እንዲሁም ያሉት ምቹ ሁኔታዎች እስመልክተው ገለፃ በማድረግ በኢትዮጵያ ኢንቨስት እንዲያደርጉ ባለሃብቶችን ጋብዟል:: ኤምባሲው ኢትዮጵያ ላይ ኢንቨስት ለማድረግ ዝግጁ ለሆኑት ኩባንያዎችም አስፍላጊውን ሁሉ ድጋፍ እንደሚያደርግ ገልፀዋል:: አክለውም ኢትዮጵያ ሰፊ የመልማት አቅም ያላት እና የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት በመሳብም ከአፍሪካ ግንባር ቀደም ተጠቃሽ አገር መሆኗን ጠቅሰው የጣልያን ኩባንያዎችም መዋዕለ ንዋያቸውን ቢያፈሱ ሰፊ የገበያ እድል እንዳአላቸውና ተጠቃሚ እንደሚሆኑም አብራርተውላቸዋል::
Twitter
Facebook
Instagram