ክብርት አምባሳደር ደሚቱ ሐምቢሳ በጣሊያን ቱሪን ከተማ የኢትዮጵያ የክብር ቆንስል ከሆኑት ኢንጂነር ፍራንኮ ሩቢኒ ጋር የስራ የእቅድ አፈፃፀም ግምገማ አደረጉ:: በእለቱ ክብርት አምባሳደር ኤምባሲው እና ክብር ቆንስሉ በፔድሞንት እያደረጉ ያለውን የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት፣ የኢንቨስትመንትና ቱሪዝም ፕሮሞሽን፣ የንግድ ትስስር እና ዳያስፖራ አገልግሎት ስራዎችን ከክብር ቆንስሉ እና ዲፕሎማቶች ጋር በመሆን ገምግመዋል። በወቅቱ የክቡር ቆንስሉ በቱሪን/ ፔድሞንት የኢትዮጵያ የክብር ቆንስል ሆነው ስራ ከጀመሩበት እ.ኤ.አ ከግንቦት 2021 ጀምሮ በተቀመጠው እቅድ መሰረት የተሰሩ ስራዎች ውጤታማ እንደሆኑ ነገር ግን ለበለጠ ውጤት የጋራ እቅድና ጥረት እንደሚያስፈልግ ተገልጿል፤ እቅዱም ተዘጋጅቶ ቀርቧል። የክቡር ቆንስል ኢንጂነር ፍራንኮ በበኩላቸው ከኤምባሲው ጋር በቅርበት በመስራት የተሻለ ውጤት ለማምጣት እንደሚተጉ ገልፀው ለስራቸው እንዲያግዛቸውም ጭምር በማሰብ ኢትዮጵያን በቅርቡ የቢዝነስ ልኡክ ይዘው ሂደው ለመጎብኘት ዝግጅት እያደረጉ እንዳሉ ገልፀዋል። በመጨረሻም ክብርት አምባሳደር የክቡር ቆንስሉን የኢትዮጵያ ጉብኝት ስኬታማ እንዲሆን ኤምባሲው ድጋፍ እንደሚያደርግላቸው ገልፀዋል፤ እንዲሁም በእቅዱ መሰረት በቀጣይ ቅድሚያ ተሰጥቶ መከናወን ስለሚገባቸው ስራዎች አቅጣጫ አስቀምጠዋል።