ዛሬ ህዳር 11 ቀን 2015 ዓ.ም ክብርት አምባሳደር ደሚቱ ሐምቢሳ በሮም ከሚገኙ የተለያዩ ከዳያስፖራ አደረጃጀት ተወካዮች ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ውይይት አድርገዋል። ውይይቱ በዋነኛነት ያተኮረው በወቅታዊ አገራዊ ጉዳዮች ላይ በተለይ በአገራችን የሰሜኑ ክፍል ያለውን ጦርነት ለመቋጨት የተደረገውን ስምምነት በተለመከተ ማብራሪያ መስጠት እና ማህበራቱ በተለያዩ ጊዜ ለአገራችን ለሚያደርጉት አወንታዊ አስተዋፅኦ ማመስገን እና ለቀጣይነቱ ድጋፍ መስጠት ላይ ያተኮረ ነበር። በውይይቱ ክብርት አምባሳደር ባለፉት ሁለት ዓመታት እንደ አገር ተጋርጦብን የነበረው አደጋ ያበቃ ዘንድ በደቡብ አፍሪካ በመንግስትና በህወሃት መካከል ስለተፈፀመው የሰላም ስምምነት፣ ስምምነቱን ለማክበር መንግስት ያለውን ቀርጠኝነት እንዲሁም በቀጣይ የወደሙ መሰረተ ልማቶችን መልሶ ለመገንባትና የአገራችንን ልማት ለማፋጠን የሁሉም ወገን ርብርብ እንደሚጠይቅ አብራረተዋል። በተጨማሪም ክብርት አምባሳደር የዳያስፖራው ማህበረሰብ ለአገራችን ላደረገው እና ለሚያደርገው ዘርፈ ብዙ ድጋፍ ከፍ ያለ ምስጋና እና ክብር አንዳላቸው በመግለፅ ለወደፊት ቀጣይነት ባለው መልኩ በአገራችን ልማት ላይ አወንታዊ አሻራ ለማሳረፍ የዳያስፖራ ማህበራቱ የሚያደርጉትን ድጋፍ አጠናከረው መቀጠል እንደላባቸው ገልፀዋል። የውይይቱ ተሳታፊዎች በበኩላቸው እናት ስትታመም አልጠይቅም የሚል ልጅ እንደሌለ ሁሉ አገራችን በጠራችን ጊዜ የተቻለንን ስናደርግ ቆይተናል አሁንም በቀጣይ ስራዎች ከአገራችን ጎን በመቆም አገራችን ለምታደርገው የልማት ጉዞ የበኩላችንን ለማበርከት ዝግጁ ነን ሲሉ ገልፀዋል።
Twitter
Facebook
Instagram