የሮም የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ኤምባሲ በተባባሪነት የተሳተፈበት 71ኛው የትሬንቶ ዓለም አቀፍ ፊልም ፌስቲባል ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት፣ ታላላቅ አርቲስቶች፣ ጋዜጠኞች፣ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ አባላት እና ሌሎች የዘርፉ ሙህራን በተገኙበት እ.ኤ.አ. ኤፕሪል 28 ቀን 2023 በትሬንቶ ከተማ በድምቀት ተከፍቷል። ምክትል ሚሲዮን መሪ አቶ አሰፋ አብዮ በመክፈቻ ዝግጅቱ ባደረጉት ንግግር ለ71ኛ ጊዜ ለሚካሄደው ይህ ታሪካዊ ፊልም ፌስቲባል ተባባሪ እንድትሆን እና ፊልም እና ዘርፈ ብዙ ባህሎቿን ለታዳሚው በስፋት እንድታቀርብ ለኢትዮጵያ እድሉ በመሰጠቱ የተሰማቸውን ደስታ የገለፁ ሲሆን የኢትዮጵያን ፊልም ታሪክና እድገት እንዲሁም የኢትዮጵያን ታሪከ ብዙነት ለታዳሚዎች አብራርተዋል። አቶ አሰፋ ጣሊያን እና ኢትዮጵያ ካላቸው ዘርፈ ብዙ ግንኙነት መካከል የባህልና የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት አንዱ መሆኑን ገልጸው መሰል ዝግጅቶች ግንኙነቱን የበለጠ እንደሚያጠናክሩት እምነታቸው እንደሆነ ገልፀዋል፤ በተጨማሪም በዝግጅቱ ደስተኛ መሆናቸውን ገልጸዋል። ከዚህ በተጨማሪ በዝግጅቱ የኢትዮጵያ እና ጣሊያን የህዝብ ለህዝብ ግንኙነትን በተመለከተ በኢትዮጵያውያን እና ጣሊያናውያን ሙህራን ገለፃ ቀርቦ ውይይት ተደርጓል። በማጠቃለያም በሶማሌኛ እና ስዋህሊ ቋንቋም ጭምር በመዝፈን የምትታወቀው ታዋቂ ትውልደ ኢትዮጵያዊት አርቲስት ሳባ አንጂላና በሙዚቃ እና ሙዚቃዊ ድራማ ስለ ኢትዮጵያ ባህል፣ እምነት፣ መልክዓምድር እና ላሊበላን የመሰሉ ታዋቂ የቱሪስት መስብ ለታዳሚው በሚገርም ዝግጅቷ አቀርባለች።
Twitter
Facebook
Instagram