ሚያዝያ 27 እና 28 ቀን 2023 ዓ.ም የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ አገልግሎት ድርጅት የስራ አፈፃፀሙን፣ የአሰራር ጉድለቶችን እና በቀጣይ በሚከናወኑ ተግባራት ማሻሻያ ግብዓት የሚረዱ ግምገማ ለመሰብሰብ ከአለም አቀፍ ወኪሎቹ ጋር አመታዊ ስብሰባ በማካሄድ ላይ ይገኛል። የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ አገልግሎት ድርጅት የመጨረሻው ዓመታዊ ስብሰባ የተካሄደው እ.ኤ.አ. በ 2019 በአዲስ አበባ እንደ ነበርና ከዚያ በኋላ በኮቪድ-19 የጉዞ ገደቦች ምክንያት ይህ ከ 4 ዓመታት በኋላ የመጀመሪያው ስብሰባ መሆኑን በመድረኩ ተገልፇል:: የመርከብ ኢንዱስትሪው አጠቃላይ እይታ፣ ባለፉት 4 ዓመታት ኮንቴይነር የማጓጓዝ አዝማሚያ፣ ዲጂታል ማድረግ እና የማጓጓዣ ቅልጥፍና በተሳታፊዎች ይቀርባል። በዓመታዊ መድረኩ ላይ የተገኙት የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር አለሙ ስሜ የጋራ ውይይትና ግምገማውን የመሩ ሲሆን የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ከዓለም አቀፍ ወኪሎቹ ጋር እያከናወነ ያለውን የሎጅስቲክ ተግባራትን የሚያሻሽሉ የስራ አቅጣጫዎች ሰጥተዋል።
