(መጋቢት 26 ቀን 2016 ዓ.ም): ተቀማጭነታቸው በሮም ሆኖ በክሮሽያ ሪፐብሊክ የኢ.ፌዲ.ሪ ልዩ መልዕክተኛና ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ክብርት ደሚቱ ሀምቢሳ በክሮሽያ የውጭና አውሮፓ ጉዳዮች ሚኒስቴር፣ የውጭ ንግድና የልማት ትብብር ጉዳዮች ምክትል ሚኒስትር ከሆኑት H.E Mr. Zdenko Lucić ጋር በኢትዮጵያና በክሮሽያ መካከል ያለውን የሁለትዮሽና የባለብዙ ወገን ግንኙነት ማጠናከርበሚያስችሉ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት አካሂደዋል። በወቅቱም ክብርት አምባሳደር ደሚቱ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ረጀም ጊዜ ያስቆጠረ መልካም ግንኙነት አውስተው፣ ሀገራቱ በኢኮኖሚ ዘርፍ ያላቸውን ትብብር ለማጠናከር መስራት እንደሚገባ ገልዋል። በሀገራችን የተካሄደውን የኢኮኖሚ ሪፎርምን በተመለከተም ለክቡር ምክትል ሚኒስትሩ ማብራሪያ ሰጥተዋል። አክለውም በሁለቱ ሀገራት የቢዝነስ ማህበረሰብ መካከል ያለውን ትብብር ለማጠናከር ሰፊ እድል ያለመሆኑን በአጽንኦት አንስተዋል። ለዚህም በሁለቱ ሀገራት የንግድ ምክር ቤቶች መካከል የሚደረግ ትብብር ወሳኝ ስለመሆኑ ገልጸዋል። ክቡር ምክትል ሚኒስትሩ በበኩላቸው በሀገራቱ መካከል ያለውን ግንኙነት ወደላቀ ደረጃ ለማሸጋገር በሀገራቸው በኩል ከፍተኛ ፍላጎት ያለ ስለመሆኑ አንስተዋል። አያይዘውም የክሮሽያ የግሉ ዘርፍ በኢትዮጵያ ያለውን ምቹ ሁኔታዎች በመጠቀም ኢንቨስት ማድረግ እንዲችል እንደሚያበረታቱም ገልጸዋል። በተያየዘም ክብርት አምባሳደር ደሚቱ በክሮሽያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ እና መካከለኛው ምስራቅ ጉዳዮች ኃላፊ እንዲሁም ከክሮሽያ የንግድ ቻምበር ዳይሬክተር ጋር ውይይት አድርገዋል። በወቅቱም በሀገራችን በሚካሄደው ″የኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፖ 2024″ ላይ የክሮሽያ ኩባንያዎች እንዲሳተፉ ግብዣ አቅርበዋል።
 
Twitter
Facebook
Instagram