(መጋቢት 26 ቀን 2016 ዓ.ም): በሮም የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ኤምባሲ አዘጋጅነት የኢትዮጵያ ንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት እና የሰርቢያ ንግድ ምክር ቤት አመራሮችና የስራ ሃላፊዎች በበይነ መረብ ውይይት ተካሄዷል፡፡ በዉይይቱ በሀገራችን ለዉጭ የኢንቨስትመንት ዕድሎች እንዲሁም ቅድሚያ የተሰጡ የኢንቨስትመንት መስኮችን በተመለከተ ገለጻ ተደርጓል። የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ኤምባሲ ምክትል ሚሲዮን መሪ የሆኑት አቶ አሰፋ አብዩ ኤምባሲያችን የሁለቱ የንግድ ም/ቤቶች መካከል ያለውን ትብብር ለማጠናከር አስፈላጊው ድጋፍ እንደሚሰጥ አረጋግጠዋል። አያይዘውም የሰርቢያ ባለሀብቶች በአገራችን በመጪው ግንቦት 2016 ዓ.ም. በሚካሄደው የኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፖ ላይ እንዲሳተፉ ጋብዘዋል። የሰርቪያ ንግድ ም/ቤት አመራሮች በበኩላቸዉ ከኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ም/ቤት ጋር በትብብር ለመስራት እንደሚፈልጉ ገልጸዋል። ይህንን ዕውን ለማድረግም በቅርቡ የንግድ ልዑክ ወደ አዲስ አበባ ለመላክ ፍላጎት ያላቸዉ መሆኑን ገልጸዋል።
 
Twitter
Facebook
Instagram