(መጋቢት 12 ቀን 2016 ዓ.ም): ክብርት ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በግሪክ ነዋሪ ከሆኑ ኢትዮጵያዊያን ጋር በተለያዩ ሀገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት አድርገዋል። በወቅቱም በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮችን አስመልክቶ ማብራሪያ የሰጡ ሲሆን ለቀረበላቸው ጥያቄዎችም ምላሽ ሰጥተዋል።
ክብርት ፕሬዝዳንት ኢትዮጵያዊያን በሚኖሩበት ሀገር የሀገራቸው አምባሳደር እንደሆኑ ገልጸው፣ ለሀገራቸው ያለምንም ልዩነት ጥብቅና መቆም እንዳለባቸው አሳስበዋል። በውጭ ነዋሪ ለሆኑ ኢትዮጵያውያን የቆንስላ አገልግሎቶችን ለመስጠት አቅም በፈቀደ መጠን ጥረት የሚደረግ መሆኑን ጠቅሰው፣ በሁሉም ሀገራት ኤምባሲ በመክፈት አገልግሎት ለመስጠት ግን የማይቻል መሆኑን ገልጸዋል። ከሌሎች ቅርብ ካሉ ኤምባሲዎች በመሸፈን የዜጎችን ጉዳይ በቅድሚያ ትኩረት አድርገው የሚሰሩ መሆኑንም አስረድተዋል። መድረኩን በጋራ የመሩት ተቀማጭነታቸው በሮም ሆኖ በግሪክ የኢፌዴሪ ልዩ መልክተኛና ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ክብርት ደሚቱ ሀሚቢሳ በበኩላቸው የሮም የሚሲዮን የአገልግሎት በግሪክ ለሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ተደራሽ ለማድረግ በየጊዜዉ በአቴንስ በመገኘት የቆንስላ አገልግሎቶች እየተሰጠ መሆኑን ገልጸዋል። አክለውም የኢትዮጵያ የክብር ቆንስል በግሪክ የመሾሙ ሂደት የተጠናቀቀ መሆኑን ጠቅሰው፣ በቅርቡም ስራ እንደሚጀምሩ ገልጸዋል።
 
Twitter
Facebook
Instagram