(መጋቢት 1 ቀን 2016) በማልታ ንግድ ጽ/ቤት ኃላፊ በሆኑት ክቡር Anton Buttigieg የተመራውና 21 አባላት ያሉት የማልታ የኢንቨስትመንትና ንግድ የልዑካን ቡድን በሀገራችን በሚካሄደው የኢንቨስትመንት ፎረም ለመሳተፍ ወደ ኢትዮጵያ አቅንቷል። የልዑካን ቡድኑ አባላት በሮም በነበራቸው ቆይታ ወቅትም ተቀማጭነታቸው በሮም ሆኖ በማልታ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ልዩ መልዕክተኛ እና ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ክብርት ደሚቱ ሀምቢሳ ለልዑካኑ ቡድኑ በኤምባሲው መኖሪያ የአሸኛኘት ፕሮግራም አድርገዋል። በወቅቱም በሀገራችን የሚኖራቸው ጉብኝትን አስመልክቶ ማብራሪያ ሰጥተዋል። በተጨማሪም የልዑካን ቡድኑ በሮም ቆይታቸው በሮም የአበበ ቢቂላ ጎዳና የሚገኘውን የጀግናው አትሌት አበበ ቢቂላ መታሰቢያ ምስለ ቅርጽን ጎብኝተዋል። የልዑካን ቡድኑ አባላት በማኑፋክቸሪንግ፣ የህክምና መሣሪያዎች ማምረት፣ በኮንስትራክሽን፣ በኢነርጂ፣ በንግድና ኢንቨስትመንት ፕሮሞሽን፤ በፋይናንስ እንዲሁም በትምህርትና ስልጠና ዘርፎች የተሰማሩ ኩባንያዎችን ያካተተ ሲሆን አባላቱ በሚሳተፉበት የቢዝነስ ፎረም ላይ ከሀገራችን አቻዎቻቸዉ ጋር የአንድ ለአንድ የቢዝነስ ውይይት ያደርጋሉ።
 
Twitter
Facebook
Instagram