128ኛው የአድዋ ድል በዓል በሮም በዓል በሮም የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ኤምባሲ የዳያስፖራ ማህበረሰብ አመራርና አባላት፣ የሃይማኖ አባቶች እና የኤምባሲው የሥራ ኃላፊዎችና ሠራተኞች በተገኙነት «ዓድዋ የጥቁር ሕዝቦች ድል! » በሚል መሪ ቃል በልዩ ድምቀት ተከብሯል፡፡ የበዓሉን አከባበር በሚመለከት ለፓናል ውይይት የመነሻ ጽሑፍ ያቀረቡት ምክትል የሚሲዮን መሪ አቶ አሰፋ አብዩ ቀደምት አባቶቻችን ከዛሬ 128 ዓመታት በፊት የጣሊያንን ወራሪ ሠራዊት ዓድዋ ላይ በታላቅ የአርበኝነት ስሜት የተቀዳጁት አንፀባራቂ ድል ለመላው ጥቁር ሕዝቦች የነፃነት ዓርማ በመሆን ከአውሮፓውያን ቅኝ ግዛት ነፃ እንዲወጡ እንዳስቻላቸው አስረድተዋል፡፡ አያይዘውም በአድዋ ድል የተገኘውን የአሸናፊነት ሥነ-ልቦና የአሁኑ ትውልድም ከድህነት ለመውጣትና አገራዊ ዘላቂ ሠላምን ለማረጋገጥ መጠቀም እንደሚገባ አጽንኦት ሰጠው አንስተዋል። በመቀጠልም በተደረገው ውይይት የአድዋ ድል በዓል ለኢትዮጵያውያን የነፃነት ቀን ሳይሆን ሉዓላዊነታችንና ብሔራዊ ክብራችንን ሊነጥቀን ከመጣ ወራሪ ኃይል ጋር በጀግንነት ተፋልመን ድል ያደረግንበትን የድል በዓል የምናከብር ታላቅ ህዝቦች መሆናችንን የምናወሳበት ሰለመሆኑ ተገልጿል። ይህም ትውልዱ በዓድዋ ድል እሴቶች እየታነፀ ታሪኩን ጠብቆ፣ ሀገርን አጽንቶ የማዝለቅ ታሪካዊ ኃላፊነቱን እየተወጣ መሆኑን በፓናል ውይይቱ ወቅት በትኩረት ተነስቷል። በመጨረሻም በሮም ኢትዮጵያውያንና ትውልደ-ኢትዮጵያውን የአድዋ ድል የኅብረ ብሔራዊ አንድነት መገለጫ፣ የጥቁር ሕዝቦች ከፍታ መሆኑን፣ በዓድዋ እሴት ድል እያስመዘገበ ሀገር ያፀናን ትውልድ መሆናችን በመገንዘብ በአገራዊ አንድነትን፣ ልማትንና በአብሮነት እጅ ለእጅ ተያይዘን የአገራችን ከፍታ ለማረጋገጥ ከመንግሥት ጎን በመሆን መሥራት አለብን በሚል የበዓሉ ታዳሚዎች ጽኑ አቋማቸውን ዳግም አረጋግጠዋል።
 
Twitter
Facebook
Instagram