የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈጻሚ መስፍን ጣሰው፣ በጣሊያን የኢትዮጵያ አምባሳደር ደሚቱ ሃምቢሳ እንዲሁም በኢትዮጵያ የጣሊያን አምባሳደር አጎስቲኖ ፓሌዝ የኤ VII የኢትዮጵያ አውሮፕላን አዲስ አበባ ስትገባ አቀባበል አድርገዋል። የአውሮፕላኗ ወደ ኢትዮጵያ መመለስ በሮም እና በአዲስ አበባ መካከል ያለውን ጥሩ ግንኙነት የሚመሰክር መልካም ማሳያ መሆኑም ተገልጿል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አውሮፕላኗ ለኢትዮጵያ እንድትመለስ ባቀረቡት ጥያቄ መሰረት ባለፈው የጣሊያን-አፍሪካ የመሪዎች ጉባኤ ላይ የጣሊያን መንግስት ለኢትዮጵያ መንግስት ማስረከቡ ይታወሳል።
 
Twitter
Facebook
Instagram