(ጥር 22 ቀን 2016 ዓ.ም): ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ላለፈው አንድ አመት ጊዜ ከጣልያን ጠቅላይ ሚኒስትር ጂኦርጂያ ሜሎኔ ጋር አውሮፕላኑ ወደ ኢትዮጵያ ስለሚመለስበት ሁኔታ ትልቅ ጥረት እና ሰፊ ንግግር ሲያደርጉ ቆይተዋል። በሮም የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ኤምባሲ አውሮፕላኑ ለኢትዮጵያ መንግሥት ማስረከብ እንዲቻል ከሚመለከታቸው የሲቪል እና ወታደራዊ ተቋማት የስራ ኃላፊዎች ጋር በመገናኘት ውይይቶች ተደርገዋል። ሚሲዮኑ የመስክ ጉብኝት በማድረግ አውሮፕላኑ ያለበትን ሁኔታ ለመገንዘብ እና በሀገራችን በኩል ስለአውሮፕላኑ በቂ መረጃ እንዲኖር በማድረግ በሚሰጠው አቅጣጫ መሰረት ተከታታይነት ያለው ክትትል ሲያደርግ ቆይቷል። የጸሐይ አውሮፕላንን ለማስመለስ መቻሉ የሀገራችንን የዲፕሎማሲያዊ ስኬቶች እንዲሁም በሁለቱ ሀገራት መካከል በተለያዩ ዘርፎች እያደገ የመጣውን የሁለትዮሽ ትብብር አመለካች ተደርጎ የሚወሰድ ነው።
 
 
Twitter
Facebook
Instagram