ዲያስፖራው የቢዝነስ ክህሎት ስለጠና እየተሰጠ ነው።
=========================
(ሰኔ 23 ቀን 2016 ዓ.ም): በሮም የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ኤምባሲ አዘጋጅነት በጣሊያን ሮምና አካባቢዋ ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ዳያስፖራ በኤምባሲው አዳራሽ የቢዝነስ ክህሎት ስልጠና እየተሰጠ ነው።
በሮም የኢፌዲሪ ኤምባሲ ምክትል ሚሲዮን መሪ አቶ አሰፋ አብዩ የስልጠናው መርሀ ግብር መክፈቻ ላይ ባደረጉት ንግግር ዳያስፖራው ከሚኖርበት አገር የሚያገኘውን ሀብት፣ ልምድ እና ዕውቀት ተጠቅሞ ተደራጅቶም ሆነ በግሉ የኢትዮጵያ መንግስት ለኢንቨስትመንት የሰጠውን ዕድል ለመጠቀም የሚያስችለውን ግንዛቤ እና የስራ ክህሎት የሚያገኝበት እንደሚሆን ገልጸዋል።
በስልጠናው ወቅት የጣሊያን ኢንተርፕርነር ደጋፊ የሆኑት ሚስተር ቪንቸንሳ የተገኙ ሲሆን የጣሊያን መንግስት ኢንተርፕሪነርን ለማበረታታት ስራ እየሰራ መሆኑንና በዘርፉ ለሚሰሩ የስልጠናና መሰል ድጋፎች እንደሚደረግ ገልፀዋል።
በስልጠናው ላይ በተለያዩ የቢዝነስ ዘርፍ ላይ እየሰሩ የሚገኙ ታዳሚዎች የተሳተፉ ሲሆን ስልጠናው ለስራ እድል ፈጠራ እና ለኢኮኖሚ እድገት አስተዋፅዖ ሊያደርጉ የሚችሉ ዲያስፖራዎችን ማፍራት የሚያስችልና ለሌሎች ተሞክሮ የሚወሰድበት እንደሚሆን ይጠበቃል።

 

Twitter
Facebook
Instagram