ክብርት አምባሳደር ደሚቱ ሀምቢሳ በግሪክ አቴንስ ከተማ ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ኮሚኒቲ አመራሮች ጋር ውጤታማ ውይይት አደረጉ። በእለቱ ወቅታዊ አገራዊ ጉዳዮችን የተወያዩ ሲሆን በቀጣይም በሰው ሰራሽም ሆነ በተፈጥሮ ችግሮች ምክንያት ጉዳት ለደረሰባቸው ድጋፍ ለሚሹ ወገኖቻችን የሚያደርጉትን ድጋፍ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ከመግባባት ላይ ተደርሷል። ክብርት አምባሳደሯ እስካሁን ድረስ በሁሉም መስክ አገራቸውን በመደገፍ ከመንግስት ጎን መቆማቸውን አመስግነው በኤምባሲው በኩል ኮሚኒቲው የሚፈልጋቸውን የቆንስላ አጋልግሎት ጥያቄ በኮሚቴ በኩል ተደራጅቶ ሲቀርብለት በየጊዜው በአቴንስ ከተማ በመገኘት አገልግሎት ለመስጠት መወሰኑን ገልፀዋል። 20 Post navigation H.E. Ambassador Demitu Hambisa hold fruitful discussion with H.E. Nikos Dendias, Greece Foreign Minister H.E. Ambassador Demitu Hambisa Confers with the President of Hellenic Republic Chamber of Commerce.