በአማራ ክልል ግብርና ቢሮ ሃላፊ ዶ/ር ሃይለማርያም ከፍያለው የተመራ የሉዑካን ቡድን በሮም የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ኤምባሲ ድጋፍ በጣሊያን ቦሎኛ እየተካሄደ በሚገኘው EIMA International Agricultural Machineries Exhibition ላይ እየተሳተፈ ይገኛል።
ሉዑካን ቡድኑ ከተሳትፎው ጎን ለጎን የተለያዩ የግብርና ማሽነሪ አምራች ኢንዱስትሪዎችን እየጎበኘ እና ወደ ኢትዮጵያ በተለይም ወደ አማራ ክልል ገብተው በጋራ መስራት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ውይይት እያደረገ ይገኛል። በዚህም መሰረት ሉዑካን ቡድኑ ህዳር 2 ቀን 2015ዓ.ም Angeloni የተባለ ታዋቂ የትራክትር ማረሻ እና መከስከሻ አምራች ኩባንያን እና Ubaldi የተባለ የግብርና ሰብሎች ዘር መዝሪያ ማሽን አምራች ኩባንያን በመጎብኘት ከኩባንያዎቹ ሃላፊዎች ጋር በስልጠና እና አቅም ግንባታ፣ በቴክኖሎጂ ሽግግር እንዲሁም ከአምባሰል ንግድ ስራች ጋር በማሸነሪ አቅርቦት በጋራ አብሮ መስራት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ውይይት አድርገዋል። ሁለቱም ድርጅቶች ምርቶቻቸውን ለኢትዮጵያ ገብያ ለማቅረብም ሆነ ከኢትዮጵያ ድርጅቶች ጋር በጋራ ማሽኖችን ለመገጣጠም ከፍተኛ ፍላጎት እንዳላቸው እና ከአማራ ክልል የቀረበውን ጥያቄ በደስታ እንደሚቀበሉት የገለፁ ሲሆን የስምምነቱን ዝርዝር ይዘት ተጨማሪ ጊዜ ወስደው ማየት እንደሚፈልጉ አብራርተዋል። በተመሳሳይ ሉዑካን ቡድኑ Schnell የተባለ የተገጣጣሚ ቤት ማሽነሪ አምራች ድርጅት የጎበኘ ሲሆን ድርጅቱ ከአሁን በፊት በክልሉ የጀመረውን ስራ እና የቴክኒክ ድጋፍ አጠናክሮ እንዲቀጥል ከድርጅቱ ሃላፊዎች ጋር በተደረገ ውይይት መግባባት ላይ ተደርሷል።

Twitter
Facebook
Instagram