‘’ የነገ ቀን ‘’ በሚል መሪ ቃል በጣሊያን ሮም እና አካባቢዋ ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ዳያስፖራዎች ጋር በመሆን አዲሱን አመት አቀባበል በድምቀት ተከበረ፣

=============================================================

(ጳጉሜ 5 ቀን 2016 ዓ.ም): በሮም የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ኤምባሲ አዘጋጅነት ‘’ የነገ ቀን ‘’ በሚል መሪ ቃል በኤምባሲው አዳራሽ በጣሊያን ሮም እና አካባቢዋ ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ዳያስፖራዎች ጋር በመሆን አዲሱን አመት ለመቀበል እለቱ በድምቀት ተከበሯል።

በፕሮግራሙ ብዙ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ዳያስፖራዎች የታደሙ ሲሆን በሮም የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ልዩ መልዕክተኛ እና ባለሙሉስልጣን አምባሳደር ክብርት አምባሳደር ደሚቱ ሀምቢሳ መልእክት አስተላልፈዋል።

በመልዕክታቸውም በመላ አገራችን ‘’ የነገ ቀን ‘’ በሚል መሪ ቃል ከህዝቡ ጋር በመሆን በሚታሰበው በዛሬው ዕለት 2016 በጀት ዓመትን እንዴት አሳለፍን ብለን የምናይበት የዓመቱ ማጠናቀቂያ እና የ2017 አዲሱን ዓመት የምንቀበልበት ዋዜማ ላይ ሆነን የምናከብረው ቀን በመሆኑ እንኳን አደረሳችሁ በማለት አገራችን በቀጣዩ አመት የተሻለችን እትዩጵያ ለትውልድ ለማስረከብ ተግተን የምንሰራበት፣ እጅ ለእጅ ተያይዘን ልማትን ለማረጋገጥ ጠንካራ ርብርብ የሚደረግበት እና በጋራ የምንቆምበት አመት ነው ብለዋል::

አያይዘውም አዲሱ አመት የሰላም፣ የፍቅር፣ የአብሮነት እና የምንበለጽግበት ጊዜ እንደሚሆን ተስፋ ያላቸው መሆኑን መልካም ምኞታቸውን ገልፀዋል።

የዳያሰፖራ ተወካዮችም በበኩላቸው ኤምባሲው ዳያስፖራው ከአገሩ ጋር ያለውን ትስስር እንዲያጠናከር እየተሰራ ያለውን ስራ አመስግነው ለመጭው አመት ለተሻለ ውጤት እንደሚተጉ አረጋግጠዋል::

 

Twitter
Facebook
Instagram