ክብርት አምባሳደር ደሚቱ ሀምቢሳ ከጀርመን አምባሳደር ጋር ተወያዩ፣
================
(መስከረም 9 ቀን 2017 ዓ.ም ): በጣሊያን የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ኤምባሲ ልዩ መልዕክተኛ እና ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ክብርት ደሚቱ ሀምቢሳ በጣሊያን የጀርመን ፌደራል ሪፐብሊክ አምባሳደር ከሆኑት Andrea Von Brandt ጋር በኤምባሲያችን ጽ/ቤት ተገናኝተው ተወያያተዋል።
በወቅቱም ክብርት አምባሳደር ከጀርመን ጋር አገራችን በጋራ ለመስራት ያላትን ፍላጎት ገልፀው፣ በሁለትዮሽ እና በባለብዙ መድረኮች ጀርመን እና ኢትዮጵያዊ ያላቸውን ረጅም ዘመን ያስቆጠረው ግንኙት አውስተው፣ ሀገራቱ ግንኙነታቸውን የበለጠ ለማጠናከር ምቹ ሁኔታ መኖሩን አንስተዋል።
ክቡር አምባሳደር Andrea Von Brand በበኩላቸው ጀርመን ከአገራችን ጋር ከጂ.አይ.ዜድ እና ከፋኦ ፕሮጀክቶቹ ጋር በተያያዘ በቀጣይም አብሮ ለመስራት ያላቸውን ፍላጎት ገልጸዋል።
H.E Ambassador Demithu Hambisa held discussion with Ambassador of Germany to Italy.
================
(September 19, 2024): H.E Ambassador Demitu Hambisa held fruitful discussion with Ambassador of Germany to Italy, H.E Ambassador Andrea Von Brandt, on issues of further strengthening the bilateral and multilateral cooperation between Ethiopia and Germany.
During their discussion, H.E Ambassador Demitu Hambisa mentioned the long-standing relationship between Germany and Ethiopia and expressed the favorable situation to further strengthen the relationship between the two countries to a higher height.
H.E Ambassador Andrea Von Brandt on his behalf expressed the interest of his country to further strengthen the existing cooperation with Ethiopia such as the implementation of GIZ and FAO projects.